ዘፍጥረት 29:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት፥ እርሷም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገረችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል ነገራት፤ እርሷም ሮጣ ሄዳ ይህንኑ ለአባቷ ነገረችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ የአባትሽ እኅት የርብቃ ልጅ ነኝ” አላት። እርስዋም ለአባቷ ልትነግር ሮጣ ሄደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት፤ እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባቷ ይህን ነገር ነገረችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም የአባትዋ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባትዋ ይህን ነገር ነገርችው። |
ይስሐቅም ያዕቆብን ላከው፥ እርሱም የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሚሆን የሶርያዊ ባቱኤል ልጅ ላባ ወዳለበት ወደ ሁለቱ ወንዞች መካከል ሄደ።