ዘፍጥረት 24:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴቲቱም ከአንተ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደሆነ ከዚህ ካቀረብሁህ መሐላ ንጹሕ ነህ፥ ልጄን ግን ወደዚያ አትመልሰው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴቲቱ ዐብራህ ወደዚህ ለመምጣት ፈቃደኛ ካልሆነች ግን ካስማልሁህ መሐላ ነጻ ትሆናለህ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትውሰደው” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጅትዋ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆን ከዚህ መሐላ ነጻ ትሆናለህ፤ ልጄን ግን በምንም ዐይነት ወደዚያ አትመልሰው።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም ከአንተ ጋር ወደዚች ምድር ለመምጣት ባትፈቅድ አንተ ከዚህ መሐላ ንጹሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደዚያ እንዳትመልሰው ተጠንቀቅ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም ከአንተ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ከዚህ ካቀረብሁህ መሐላ ንጽሕ ነህ፤ ልጄን ግን ወደዚያ አትመልሰው። |
ባልዋ ግን በሰማበት ቀን ቢከለክላት፥ በእርሷ ላይ ያለውን ስእለትዋን ከአንደበትዋም በችኮላ ተናግራ ራስዋን በመሐላ ያሰረችበትን ነገር ከንቱ ያደርገዋል፤ ጌታም ይቅር ይላታል።