ዘፍጥረት 24:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው፥ ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጉድጓዱ ሮጠች፥ ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈጥናም በእንስራው ውስጥ የነበረውን ውሃ በገንዳ ውስጥ ገለበጠች፤ እየሮጠች ከጕድጓዱ ውሃ እያመላለሰች ግመሎቹ እስኪበቃቸው ድረስ አጠጣቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወዲያውኑ በእንስራዋ የያዘችውን ውሃ ግመሎቹ በሚጠጡበት ገንዳ ላይ ገልብጣ ግመሎቹ ሁሉ ጠጥተው እስከሚረኩ ድረስ እየተጣደፈች ከጒድጓድ ውሃ መቅዳት ቀጠለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው፤ ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጕድጓዱ ሮጠች፤ ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጕድጓዱ ሮጠች ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች። |
ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥