ዘፍጥረት 22:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጁንም ዘርግቶ፥ ልጁን ለማረድ አብርሃም ቢላዋ አነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ልጁን ለማረድ እጁን ዘርግቶ ቢላዋውን አነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንሥቶ እጁን ዘረጋ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም እጁን ዘረጋ፤ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም እጁን ዘረጋ፥ ልጁንም ያርድ ዘንድ ቢላዋ አነሣ። |
እግዚአብሔር ወዳለውም ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠራና እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ በመሠዊያው ላይ፥ ከእንጨቱ በላይ አጋደመው።