የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፥ ጌታ እግዚአብሔር፥ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፥ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።
ዘፍጥረት 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአዳም የወሰዳትንም አጥንት፥ ጌታ እግዚእብሔር፥ ሴት አድርጎ ሠራት፥ ወደ አዳምም አመጣለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም የወሰዳትን ዐጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ጐን የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚእብሔር አምልስክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት ወደ አዳምም አመጣት። |
የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ፥ ጌታ እግዚአብሔር፥ ከምድር ፈጠረ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፥ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ።