አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባርያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።
ዘፍጥረት 16:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ወደ አጋር ገባ፥ አረገዘችም፥ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እመቤትዋን በዓይንዋ አቃለለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራምም ከአጋር ጋራ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች። አጋርም ነፍሰ ጡር መሆኗን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን መናቅ ጀመረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም ወደ አጋር ገባ፤ ፀነሰችም፤ አጋር መፅነስዋን ባወቀች ጊዜ በእመቤትዋ ላይ ኮራች፤ ናቀቻትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብራምም ወደ አጋር ገባ፤ ፀነሰችም፤ እንደ ፀነሰችም ባየች ጊዜ እመቤቷን ማክበርዋን ተወች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ወደ አጋር ገባ፥ አረገዘችም፤ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እመቤትዋን በዓይንዋ አቃለለች። |
አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር ዐሥር ዓመት ከተቀመጠ በኋላ፥ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባርያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።
ሦራም አብራምን፦ መገፋቴ በአንተ ላይ ይሁን፥ እኔ ባርያዬን በጉያህ ሰጠሁህ፥ እንዳረገዘችም ባየች ጊዜ እኔን በዓይንዋ አቃለለችኝ፥ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ አለችው።
የጌታ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፥ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በጌታ ፊት ሲዘልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው።
ወንድሞች ሆይ! ስለ አንዱ በሌላው ላይ አንዳችሁም እንዳትታበዩ “ከተጻፈው አትለፍ፤” የሚለውን በእኛ እንድትማሩ፥ በዚህ ስለ እናንተ ስል ራሴንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ ተናገርሁ።