የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያ በኋላ ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፥ ከተማይቱንም መሥራት አቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ በታተናቸው፤ ከተማዋንም መሥራት አቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማውንም መሥራት አቆሙ፤

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቋን​ቋ​ቸ​ውን ለያየ፤ ከዚ​ያም በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ በተ​ና​ቸው፤ ከዚ​ያም በኋላ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና ግን​ቡን መሥ​ራ​ትን ተዉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 11:8
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዔቦር ሁለት ልጆች ወለደ፤ አንደኛው እርሱ በተወለደበት ዘመን ሕዝቦች ስለ ተከፋፈሉ ፋሌቅ ተባለ፤ ሌላው ዮቅጣን ይባል ነበር።


ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች፥ እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ሁሉም የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።


ከእነዚህም በባሕር ዳርቻ ሕዝቦች፥ ሁሉም በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፍለው የሚኖሩ የያፌት ልጆች ዘር ናቸው።


እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።


ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን ተባለ።


ቁጣቸው ርጉም ይሁን፥ ጽኑ ነበርና፥ ኩርፍታቸውም፥ ብርቱ ነበርና፥ በያዕቆብ እከፋፍላቸዋለሁ፥ በእስራኤልም እበታትናቸዋለሁ።


ጌታ የአሕዛብን ምክር ያጠፋል፥ የአሕዛብንም አሳብ ይመልሳል።


አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘለዓለም ልዑል ነህ፥


በክንዱ ኃያል ሥራን ሠርቶአል፤ በልባቸው የሚታበዩትን በትኖአል፤


ልዑል ለአሕዛብ ርስታቸውን ባወረሰ ጊዜ፥ የሰውን ልጆች በለየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቍጥር የአሕዛብን ድንበር አቆመ።