ዘፍጥረት 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ፥ ሞተም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ 430 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔቦርም ፋሌቅን ከወለደ በኋላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ፤ ሞተም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፋሌቅንም ወለደ፤ ዔበርም ፋሌቅን ከወለደ በኍላ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፥ ወንዶችንም ሴቶችንም ወለደ ሞተም። |