ዘፍጥረት 11:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴም ትውልድ ይህ ነው። ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት ሴም መቶ ዓመት በሆነው ጊዜ፥ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሴም ትውልድ ይህ ነው፦ ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሴም ዘሮች የሚከተሉት ናቸው፦ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሁለት ዓመት ቈይቶ ሴም 100 ዓመት በሆነው ጊዜ አርፋክስድ የተባለ ልጅ ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም ከጥፋት ውኃ በኋላ በሁለተኛው ዓመት አርፋክስድን በወለደ ጊዜ የመቶ ዓመት ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴም ትውልድ ይህ ነው። ሴም የመቶ ዓመት ሰው ነበረ፥ አርፋክስድንም ከጥፋት ውኃ በኍላ በሁለተኛው ዓመት ወለደ። |