ሕዝቅኤል 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ጥቂት ውሰድ፥ በመጐናጸፊያህም ቋጥራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም ከጠጕሮቹ ጥቂት ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ቋጥር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በከተማው ዙሪያ በሰይፍ ቈራርጠው፤ ደግሞም ከዚሁ ጥቂት ጠጒር ወስደህ በመጐናጸፊያህ ጫፍ ላይ ቋጥረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በቍጥር ጥቂቶቹን ውሰድ፤ በመጐናጸፊያህም ቋጥራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በጥቂቱ ውሰድ በመጐናጸፊያህም ጫፍ ቋጥራቸው። |
የመከበብም ወራት ሲፈጸም አንድ ሦስተኛውን በከተማይቱ መካከል በእሳት ታቃጥለዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወስደህ ዙሪያውን በሰይፍ ትመታዋለህ፥ አንድ ሦስተኛውን ወደ ነፋስ ትበትነዋለህ፥ እኔም ከኋላቸው ሰይፍ እመዝዛለሁ።