ዘዳግም 8:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእነዚህ አርባ ዓመታት የለበስኸው ልብስ አላረጀም፥ እግርህም አላበጠም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእነዚህ አርባ ዓመታት ውስጥ ልብስህ አላለቀም፤ እግርህም አላበጠም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚህም አርባ ዓመቶች ውስጥ ልብስህ አላለቀም፤ ከጒዞም የተነሣ እግርህ አላበጠም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የለበስኸው ልብስ አላረጀም፤ እግርህም አልነቃም፤ እነሆ፥ አርባ ዓመት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእነዚህ አርባ ዓመታት የለበስኸው ልብስ አላረጀም፥ እግርህም አላበጠም። |
“ጌታ አምላክህ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና፥ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መሄድህን አውቆአል፥ በዚህ አርባ ዓመት ውስጥ ጌታ አምላክህ ከአንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አላጣህም።