ምሽጎቹንም ከተሞች የሰባውንም ምድር ወሰዱ፥ መልካሙን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጉድጓዶች፥ ወይኖቹንና ወይራዎቹን ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፥ በሉም፥ ጠገቡም፥ ወፈሩም፥ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።”
ዘዳግም 3:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ሁሉ ከተሞች፥ በቅጥር ካልተመሸጉት ከእጅግ ብዙ ከተሞች ሌላ፥ ቁመቱ ረጅም በሆነ ቅጥር በመዝጊያና በመወርወሪያም የተመሸጉ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ከተሞች ሁሉ ከፍ ባሉ ቅጥሮች፣ በመዝጊያዎችና በመወርወሪያዎች የተመሸጉ ነበሩ፤ እንዲሁም ቅጥር የሌላቸው አያሌ መንደሮች ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ሁሉ ከተሞች ከፍ ያለ ቁመት ባላቸው ቅጽሮች የተመሸጉ ነበሩ፤ የቅጽሮቹም በሮች በመወርወሪያ የሚዘጉ ነበሩ፤ ቅጽር የሌላቸው ብዙ መንደሮችም ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅግ ብዙ ከሆኑት ከፌርዜዎን ከተሞች ሌላ፥ እነዚህ ከተሞች ሁሉ ቁመቱ ረዥም በሆነ ቅጥር በመዝጊያና በመወርወሪያም የተመሸጉ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቅጥር ካልተመሸጉት ከእጅግ ብዙ ከተሞች ሌላ፥ እነዚህ ከተሞች ሁሉ ቁመቱ ረጅም በሆነ ቅጥር በመዝጊያና በመወርወሪያም የተመሸጉ ነበሩ። |
ምሽጎቹንም ከተሞች የሰባውንም ምድር ወሰዱ፥ መልካሙን ነገር የሞሉትን ቤቶች፥ የተማሱትንም ጉድጓዶች፥ ወይኖቹንና ወይራዎቹን ብዙዎቹንም የፍሬ ዛፎች ወረሱ፥ በሉም፥ ጠገቡም፥ ወፈሩም፥ በታላቅ በጎነትህም ደስ አላቸው።”
ወዴትስ እንወጣለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል፥ ከተሞቹም ታላላቆች የተመሸጉም እስከ ሰማይም የደረሱ ናቸው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፥’ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን አወኩት።
ያን ጊዜም ከተሞቹ ሁሉ ያዝን፥ የአርጎብን ግዛቶች ሁሉ፥ ከሥልሳ ከተሞች ጋር፥ በባሳን ያለውን የዖግን መንግሥት፥ ያልወሰድነው ምንም ከተማ አልነበረም።
የወርቅ ዐይጦቹም ቍጥር፥ አምስቱ የፍልስጥኤም ገዢዎች በሚያስተዳድሯቸው የተመሸጉ ከተሞችና ከእነዚህ ውጭ ባሉት መንደሮቻቸው ቍጥር ልክ ነው። በቤትሼሜሻዊው በኢያሱ እርሻ ውስጥ የጌታን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ትልቅ ቋጥኝ እስከ ዛሬ ምስክር ነው።