ዘዳግም 2:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘በአገርህ ላይ ልለፍ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳልል አውራ ጎዳናውን ይዤ እሄዳለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በአገርህ አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን፤ ከዋናው መንገድ አንወጣም፤ ቀኝም ግራም አንልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘በእናንተ አገር በኩል አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ ከመንገዱ ሳንወጣና ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሳንል በቀጥታ እንሄዳለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ‘በሀገርህ ላይ ልለፍ፤ በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአውራ ጎዳና እሄዳለሁ፥ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አልተላለፍም። |
“ከዚያም እስራኤል በሐሴቦን ወዳለው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞች ልኮ፥ ‘ወደ ገዛ ስፍራችን ለመሄድ በአገርህ እንዳልፍ ፍቀድልኝ’ አለው።