ዘዳግም 1:43 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ተናገርኋችሁ፥ እናንተ ግን በጌታ ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፥ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም ነገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አላደመጣችሁም፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐምፃችሁ፣ በትዕቢታችሁ ወደ ተራራማው አገር ዘመታችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያለኝንም ለእናንተ ነገርኳችሁ፤ እናንተ ግን እምቢተኞች ሆናችሁ፤ በእርሱም ላይ ዐምፃችሁ በትዕቢታችሁ ብዛት ወደ ኮረብታማይቱ አገር ዘመታችሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ተላለፋችሁ፤ በኀይላችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዓመፃችሁ እንጂ አልሰማችሁም፤ በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ። |
በማግስቱም ማልደው ተነሡ፥ ወደ ተራራውም ራስ እንዲህ እያሉ ወጡ፦ እነሆ፥ እኛ በዚህ አለን፤ እኛ ኃጢአትን ሠርተናልና ጌታ ወዳለው ስፍራ እንወጣለን።
ነገር ግን የአገሩ ተወላጅ ቢሆን ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በትዕቢት ማናቸውንም ነገሮች የሚያደርግ ሰው ጌታን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።
“እናንተ አንገተ ደንዳኖች ልባችሁና ጆሮአችሁም ያልተገረዘ፤ እናንተ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንደ ተቃወሙት እናንተ ደግሞ።
አምላክህን ጌታን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህኑን ወይም ፈራጁን ባለመታዘዝ የሚዳፈር፥ ያ ሰው ይሙት፥ ከእስራኤልም መካከል ክፋትን አስወግድ፥