ዘዳግም 1:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይፉኔ ልጅ ከካሌብ በቀር፤ እርሱ ያያታል፥ የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ፥ ምክንያቱም ጌታን ፈጽሞ ተከትሎአል።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር የሚያያት የለም፤ እርሱ ያያታል፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ስለ ተከተለ፣ የረገጣትን ምድር ለርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚያች ምድር መግባት የሚችል የይፉኔ ልጅ ካሌብ ብቻ ነው፤ እርሱ በፍጹም ልቡ ታማኝ ሆኖ ስለ ተገኘ ያቺን የጐበኛትን ምድር ለእርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በስተቀር፥ እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ፥ ለልጆቹም እሰጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር እርሱ ግን ያያታል፤ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱ ለልጆቹም እሰጣለሁ ብሎ ማለ። |
ጌታ ስለ እነርሱ፦ “በእውነት በምድረ በዳ ይሞታሉ” ብሎ ተናግሮአልና። ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ ከነዌም ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳ አልቀረም።