ዘዳግም 1:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገሩ መልካም ሆኖ ታየኝ፥ ከእናንተም ዐሥራ ሁለት ሰው መረጥሁ፥ ከየነገዱ ሁሉ አንዳንድ ሰው ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ሐሳብ መልካም መስሎ ታየኝ፤ እኔም ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሰው በማድረግ ከእናንተ ዐሥራ ሁለት ሰዎች መረጥሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ይህንንም ማድረግ መልካም መስሎ ስለ ታየኝ ከእያንዳንዱ ነገድ አንዳንድ ሰው በመምረጥ ዐሥራ ሁለት ሰዎችን ላክሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ነገር ደስ አሰኘኝ፤ ከእናንተም ዐሥራ ሁለት ሰው ወሰድሁ፤ ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ነገር ደስ አሰኘኝ፤ ከእናንተም አሥራ ሁለት ሰው መረጥሁ፤ ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው ነበረ። |
“እናንተም ሁላችሁ ወደ እኔ ቀርባችሁ፦ ‘ምድሪቱን እንዲሰልሉልንና እንወጣባት ዘንድ የሚገባንን የመንገዱንና የምንገባባቸውን የእነዚያን ከተሞች ወሬ ተመልሰው እንዲነግሩን በፊታችን ሰዎች እንላክ’ አላችሁኝ።