ቈላስይስ 4:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮስጦስም የተባለ ኢያሱ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል፤ ከተገረዙትም ወገን የሆኑ፥ በእግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮስጦስ የተባለው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙት መካከል ለእግዚአብሔር መንግሥት ዐብረውኝ የሚሠሩት፣ እኔንም ያጽናኑኝ እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም አጽናንተውናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮስጦስ ተብሎም የሚጠራው ኢያሱ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው ከሚሠሩት ሰዎች መካከል የአይሁድ ወገኖች የሆኑት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮስጦስ የተባለ ኢያሱም፥ ከግዙራን ሰዎች ወገን የሚሆኑ እነዚህ ሰላም ይሏችኋል። በእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ረዳቶች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እነርሱም እኔን አጽናንተውኛል። |
ለተገረዙትም አባት ነው፤ ለተገረዙት ብቻ ሳይሆን፥ ነገር ግን አባታችን አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነቱን ፈለግ ለሚከተሉ ጭምር ነው።
ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በአካል ላይ በሰው እጅ ከተደረገው የተነሣ፥ “ተገርዘናል” በሚሉት፥ “ያልተገረዛችሁ” የተባላችሁትን ያን አስታውሱ፤
አንተም ደግሞ በሥራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ! ከእኔ ጎን በመቆም ከቀለሜንጦስ ጋር አብረው በወንጌል ሥራ ተጋድለዋልና እነዚህን ሴቶችና የተቀሩትን በሕይወት መጽሐፍ የተጻፉትን ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩትን እንድትረዱአቸው እለምንሃለሁ።
ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን፥ የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤