አሞጽ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሜንጦ፥ ትሩፋቶቻችሁንም በመንጠቆ የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሏል፤ “እነሆ፤ በመንጠቆ ተይዛችሁ የምትወሰዱበት ትሩፋናችሁ እንኳ፣ በዓሣ መንጠቆ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር በቅድስናው እንዲህ ሲል ምሎአል፦ “እናንተ በመንጠቆ ተይዞ እንደሚወሰድ ነገር የምትወሰዱበት ጊዜ ይመጣል፤ ከእናንተ እስከ መጨረሻ የቈዩት እንኳ በመንጠቆ ተይዘው እንደሚወሰዱ ዐሣዎች ይወሰዳሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታ አግዚአብሔር፥ “እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን እነሆ በላያችሁ ይመጣል” ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታ እግዚአብሔር፦ እናንተን በሰልፍ ዕቃ፥ ቅሬታችሁንም በመቃጥን የሚወስዱበት ቀን፥ እነሆ፥ በላያችሁ ይመጣል ብሎ በቅዱስነቱ ምሎአል። |
“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ፥ ይላል ጌታ፥ እነርሱም ያጠምዱአቸዋል፤ ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እልካለሁ፥ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያድኑአቸዋል።
በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፥ የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋር አጣብቃለሁ፤ በቅርፊትህ ከተጣበቁት የወንዞችህ ዓሦች ሁሉ ጋር ከወንዞችህ መካከል አወጣሃለሁ።
የጠፋውን እፈልጋለሁ፥ የባዘነውን እመልሳለሁ፥ የተሰበረውንም እጠግናለሁ የደከመውንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን አጠፋለሁ፤ በፍትሕም እጠብቀዋለሁ።
ወደ ኋላ እመልስሃለሁ፥ መንጠቆ በመንጋጋህ አስገባሃለሁ፥ አንተንና ሠራዊትህን ሁሉ፥ ፈረሶችን፥ ፈረሰኞችን፥ የጦር ልብስ የለበሱትን ሁሉ፥ ሁሉም ሰይፍ የያዙ ጋሻና ራስ ቁርን ካደረጉ ታላቅ ጉባኤ ጋር አወጣሃለሁ፥
ጌታ እግዚአብሔር፦ “የያዕቆብን ትዕቢት ተጸይፌአለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ጠልቻለሁ፤ ስለዚህ ከተማይቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ አሳልፌ እሰጣለሁ” ብሎ በራሱ ምሎአል፥ ይላል ጌታ የሠራዊት አምላክ።