ሐዋርያት ሥራ 7:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ እናንተ ዛሬ ወደምትኖሩባት ወደዚች አገር አወጣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም ከከለዳውያን ምድር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከአባቱም ሞት በኋላ፣ አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት ወደዚህ አገር አመጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ፤ አባቱ ከሞተ በኋላም እግዚአብሔር ከካራን አውጥቶ ዛሬ እናንተ ወደምትኖሩባት አገር አመጣው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ ከከለዳውያን ሀገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ፤ ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ፥ ዛሬ እናንተ ወደ አላችሁባት ወደዚች ሀገር አመጣው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ጊዜ ከከለዳውያን አገር ወጥቶ በካራን ተቀመጠ። ከዚያም አባቱ ከሞተ በኋላ እናንተ ዛሬ ወደምትኖሩባት ወደዚች አገር አወጣው። |
ከምሥራቅ አንዱን ያስነሣ፥ በጽድቅም ወደ እግሩ የጠራው ማን ነው? አሕዛብንም አሳልፎ በፊቱ ሰጠው፥ ነገሥታትንም አስገዛለት፤ ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አድርጎ ሰጣቸው።