ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላም ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ ገባች።
ሦስት ሰዓት ያህልም ካለፈ በኋላ፣ ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ መጥታ ገባች።
ከሦስት ሰዓት ያኽል በኋላ የሐናንያ ሚስት በባልዋ ላይ የደረሰውን ሁናቴ ሳታውቅ መጣች።
ይህም ከሆነ ከሦስት ሰዓት በኋላ ሚስቱ መጣች፤ ባልዋም የሆነውን ሳታውቅ ገባች።
ጐበዞችም ተነሥተው ከፈኑት፤ አውጥተውም ቀበሩት።
ጴጥሮስም መልሶ “እስቲ ንገሪኝ፤ መሬታችሁን ይህን ለሚያህል ሸጣችሁትን?” አላት። እርሷም “አዎን፤ ይህን ለሚያህል ነው፤” አለች።