2 ሳሙኤል 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “የት ነው ያለው?” ብሎ ጠየቀ። ጺባም፥ “ሎደባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “የት ነው ያለው?” ብሎ ጠየቀ። ሲባም፣ “ሎደባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “የት ነው ያለው?” ሲል ጠየቀ። ጺባም “በሎደባር በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ሲል መለሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ወዴት ነው?” አለው፤ ሲባም ለንጉሡ፥ “እነሆ እርሱ በሎዶባር በአብያል ልጅ በማኪር ቤት አለ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ወዴት ነው? አለው፥ ሲባም ንጉሡን፦ እነሆ፥ እርሱ በሎዶባር በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት አለ አለው። |