2 ሳሙኤል 24:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ሲዶና ዞሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አዳሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገለዓድም አዳሳይ ወደምትባል ወደ ተባሶን ሀገርም መጡ፤ ወደ ዳኒዳንና ወደ ኡዳንም ደረሱ፤ ወደ ሲዶናም ዞሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ገለዓድም ወደ ተባሶን አዳሰይ አገር መጡ፥ ወደ ዳንየዓንም ደረሱ፥ ወደ ሲዶናም ዞሩ፥ |
የሮቤልና የጋድ ልጆችም እጅግ ብዙ እንስሶች ነበሩአቸው፤ እነሆም፥ የኢያዜር ምድርና የገለዓድ ምድር ለእንስሶች የተመቸ ስፍራ እንደ ነበረ ባዩ ጊዜ፥
ጌታም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ መቱአቸውም፥ ወደ ታላቂቱም ሲዶና፥ ወደ ማሴሮንም፥ በምሥራቅም በኩል ወዳለው ወደ ምጽጳ ሸለቆ አሳደዱአቸው፤ አንድም ሳያስቀሩ መቱአቸው።
የዳንም ልጆች ግዛታቸውን መቆጣጠር ባለልቻሉ ጊዜ ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ሌሼም የነበረውን ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት።