ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና አብረውት የነበሩትን የጦር አዛዦች፥ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ ስለምፈልግ ሕዝቡን ቁጠሩ።” አላቸው።
2 ሳሙኤል 24:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ጌታ ከዚያች ዕለት ጥዋት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ ሰው አለቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚያች ዕለት ጧት አንሥቶ እስከ ተወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ መቅሠፍት ላከ፤ በዚህም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺሕ ሰው ዐለቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ከዚያን ጠዋት ጀምሮ እስከ ወሰነው ቀን ድረስ በእስራኤል ላይ ቸነፈር አመጣ፤ በሀገሪቱ ዳር እስከ ዳር ማለትም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ሰባ ሺህ እስራኤላውያን አለቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፤ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ጌታ ከጥዋት እስከ ቀትር ቸነፈርን በእስራኤል ላይ ላከ። ቸነፈሩም በሕዝቡ መካከል ጀመረ፤ ከሕዝቡም ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ሰባ ሺህ ሰው ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ቸነፈሩን መረጠ፥ የስንዴም መከር ወራት በሆነ ጊዜ ቸነፈሩ በሕዝቡ መካከል ጀመረ፥ ከሕዝቡም ሰባ ሺህ ሰው ሞተ። |
ስለዚህም ንጉሡ ኢዮአብንና አብረውት የነበሩትን የጦር አዛዦች፥ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወዳሉት የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፤ ምን ያኽል ሕዝብ እንዳለ ማወቅ ስለምፈልግ ሕዝቡን ቁጠሩ።” አላቸው።
የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ መቁጠር ጀመረ፥ ነገር ግን አልፈጸመም፤ ስለዚህም በእስራኤል ላይ ቁጣ ወረደ፥ ቁጥራቸውም በንጉሡ በዳዊት መዝገብ አልተጻፈም።
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።
አየሁም፤ እነሆም የገረጣ ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ነበረ። ሲኦልም ተከተለው፤ በሰይፍና በራብም በሞትም በምድርም አራዊት ይገድሉ ዘንድ ከምድር በአራተኛዋ እጅ ላይ ሥልጣን ተሰጣቸው።
ጌታም ከቤትሼሜሽ ሰዎች ጥቂቱን መታ፤ ምክንያቱም ወደ ጌታ ታቦት ውስጥ በመመልከታቸው ነበር። ከመካከላቸው ሰባ ሰዎችን ገደለ፤ ጌታ እጅግ ስለ መታቸውም ሕዝቡ አለቀሱ።