አሞናውያን፥ ዳዊት እንደጠላቸው ባወቁ ጊዜ፥ ከቤትረሖብና ከጾባ ሃያ ሺህ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም ንጉሥ መዓካን ከአንድ ሺህ ሰዎቹ ጋር ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።
2 ሳሙኤል 23:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤሊፌሌጥ፥ የጊሎናዊው የአሒጦፌል ልጅ ኤሊአም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የማዕካታዊው የአሐስባይ ልጅ ኤሌፋላት፣ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊአም፣ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመካኪ ልጅ የአሶብ ልጅ ኤላፍላት፥ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤልያብ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሮዳዊው የአራር ልጅ አምናን፥ የማዕካታዊው ልጅ የአሐስባይ ልጅ ኤሌፋላት፥ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤልያብ፥ |
አሞናውያን፥ ዳዊት እንደጠላቸው ባወቁ ጊዜ፥ ከቤትረሖብና ከጾባ ሃያ ሺህ ሶርያውያን እግረኛ ወታደሮችን እንዲሁም ንጉሥ መዓካን ከአንድ ሺህ ሰዎቹ ጋር ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።
አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ተሰለፉ፤ የጾባና የረሖብ ሶርያውያን እንዲሁም የጦብና የመዓካ ሰዎች ለብቻ ሜዳው ላይ ተሰለፉ።
አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ የሆነው ጊሎአዊው አኪጦፌል ከአገሩ ከጊሎ ወደ እርሱ እንዲመጣ ላከበት፤ ስለዚህ ሤራው ጥንካሬ አገኘ፤ የአቤሴሎምም ተከታዮች ቍጥር እየበዛ ሄደ።
በዚህ ጊዜ፥ “ከአቤሴሎም ጋር ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ “ጌታ ሆይ! እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ሲል ጸለየ።
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ሼባዕም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል ዐልፎ ወደ አቤል ቤት ማዓካ ወደ መላው የቢክሪያውያን ግዛት መጣ፤ የቢክሪ ሰዎችም ተሰብስበው ተከተሉት።
የምናሴ ልጅ ያኢር፥ ባሳንን እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ፥ የአርጎብን ግዛት ሁሉ ወሰደ፥ ይችንም የባሳን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ በሚጠራበት የያኢር መንደሮች ብሎ ጠራ።
ዳዊትም ሒታዊውን አቢሜሌክንና የጸሩያን ልጅ የኢዮአብን ወንድም አቢሳን፥ “ወደ ሳኦል ሰፈር አብሮኝ የሚወርድ ማነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሳም፥ “እኔ አብሬህ እወርዳለሁ” አለ።