2 ሳሙኤል 22:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሞት ሞገድ ከበበኝ፤ የጥፋትም ጐርፍ አጥለቀለቀኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ ምናምንቴ ነገርም አጥለቀለቀኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤ የዐመፅ ጎርፍም አስፈራኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፥ |
እነርሱም፦ “ሰላምና ደኅንነት ነው” በሚሉ ጊዜ ምጥ እንደ ያዛት እርጉዝ ሴት ድንገተኛ ጥፋት በእነርሱ ላይ ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።
ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ሴት ፍርድ አሳይሃለሁ፤