2 ሳሙኤል 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማሳይ ይሁዳን ለመጥራት ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከወሰነው ጊዜ በላይ ቆየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜሳይ ይሁዳን ለመጥራት ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ ከወሰነው ጊዜ በላይ ቈየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐማሣም ሊጠራቸው ሄደ፤ ነገር ግን ንጉሡ በቀጠረው ቀን ተመልሶ ሊመጣ አልቻለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜሳይም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፤ ነገር ግን ዳዊት የቀጠረውን ቀን አሳልፎ ዘገየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜሳይም የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ይጠራ ዘንድ ሄደ፥ ነገር ግን እርሱ የተቀጠረውን ቀን አሳልፎ ዘገየ። |
ዳዊትም አቢሳን፥ “ከአቤሴሎም ይልቅ አሁን የቢክሪ ልጅ ሼባዕ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስብን ስለሆነ የጌታህን አገልጋዮች ይዘህ አሳደው፤ ያለዚያ የተመሸገ ከተማ አግኝቶ ያመልጠናል” አለው።