ኢዮአብ ወደ እርሷ ቀረበ፤ እርሷም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፥ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን አድምጥ” አለችው። እርሱም፥ “እያዳመጥኩ ነው” አላት።
2 ሳሙኤል 20:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በመቀጠልም እንዲህ አለች፤ “በቀድሞው ጊዜ ሰዎች፥ ‘ምክርን ከአቤል ጠይቁ’ ይሉ ነበር፤ ነገሩም እንዳሉት ይፈጸም ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በመቀጠልም እንዲህ አለች፤ “በቀድሞው ጊዜ ሰዎች፣ ‘ምክርን ከአቤል ጠይቁ’ ይሉ ነበር፤ ታዲያ እንዳሉትም ይፈጸም ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እንዲህ አለችው፤ “በድሮ ዘመን ‘ወደ አቤል ከተማ ሄዳችሁ የጥያቄአችሁን መልስ ከዚያ ታገኛላችሁ’ ይባል ነበር፤ ሰዎችም የሚያደርጉት ይህንኑ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም እንዲህ አለች፥ “የቀደሙ ሰዎች በእስራኤል ዘንድ አማኞች በሚያስቡት ነገር ተሳስተው እንደ ሆነ በአቤልና በዳን በእውነት ይጠይቁ ይባል ነበር፤ በርግጥም በዚህ ዐይነት ነገር ከተሳሳቱ በአቤል ይጠይቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ ቀድሞ፦ የሚጠይቅ በአቤል ዘንድ ይጠይቅ ይባል ነበር፥ እንዲሁም ነገሩ ይፈጸም ነበር። |
ኢዮአብ ወደ እርሷ ቀረበ፤ እርሷም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርሷም፥ “እንግዲህ አገልጋይህ የምትለውን አድምጥ” አለችው። እርሱም፥ “እያዳመጥኩ ነው” አላት።
በእስራኤል ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ እኔ ነኝ፤ አንተ በእስራኤል እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት ትሻለህ፤ የጌታን ርስት ለመዋጥ የፈለግኸው ለምንድን ነው?”