2 ሳሙኤል 2:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም አበኔር፥ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ ምርኮውን ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አበኔር፣ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጕልማሳ ይዘህ መሣሪያውን ንጠቀው” አለው። አሣሄል ግን እርሱን መከታተሉን አልተወም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔርም “እኔን ማሳደድ ተው! ይልቅስ ከወታደሮቹ አንዱን በማሳደድ የያዘውን ምርኮ ውሰድ” አለው፤ ዐሣሄል ግን እርሱን ማሳደዱን ቀጠለ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብላቴኖቹም አንድ ጐልማሳ ያዝ፤ መሣሪያውንም ለራስህ ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም፦ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፥ አንድ ጕልማሳ ያዝ፥ መሣርያውንም ውስድ አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ። |
እንደገናም አበኔር፥ “እኔን ማሳደድህን ተው! እኔስ ስለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት እንዴት ብዬ አያለሁ?” አለው።
ከዚያም የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት፤ ወደ አስቀሎናም ወርዶ ከሰዎቻቸው መካከል ሠላሳውን ገደለ፤ ያላቸውንም ከገፈፈ በኋላ ልብሶቻቸውን አምጥቶ እንቈቅልሹን ለፈቱት ሰዎች ሰጣቸው። በቁጣ እንደነደደም ተነሥቶ ወደ አባቱ ቤት ወጣ።