2 ሳሙኤል 19:41 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡ ወደ ጌልገላ ሲሄድ፥ ኪምሃም አብሮት ሄደ። የይሁዳ ሠራዊት በሙሉ እንዲሁም ግማሹ የእስራኤል ሠራዊት ንጉሡን አጅበው አሻገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው፣ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ንጉሡን በሹልክታ ለብቻቸው ይዘው እርሱንና ቤተ ሰውን ከተከታዮቹ ጋራ ዮርዳኖስን ለምን አሻገሩ?” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ ንጉሡ ቀርበው “ንጉሥ ሆይ! ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች አንተን ወስደው የራሳቸው ለማድረግ፥ እንዲሁም አንተንና ቤተሰብህን፥ ተከታዮችህንም ሁሉ አጅበው የዮርዳኖስን ወንዝ ለማሻገር መብት እንዳላቸው ስለምን ያስባሉ?” ሲሉ ጠየቁት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጡ፤ ንጉሡንም፥ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ለምን ሰረቁህ? ንጉሡንም ቤተ ሰቡንም ዮርዳኖስን አሻገሩ። የዳዊትም ሰዎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሥ መጡ፥ ንጉሡንም፦ ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች ለምን ሰረቁህ? ንጉሡንም ቤተ ሰቡንም ከእርሱም ጋር የዳዊትን ሰዎች ሁሉ ዮርዳኖስን አሻገሩ? አሉት። |
ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፤ “የእስራኤል ሽማግሌዎችን እንዲህ በሏቸው አለ፤ ‘በመላው እስራኤል የሚባለው ሁሉ ለንጉሡ ባለበት የደረሰው ስለሆነ፥ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እንዴት የመጨረሻ ሰዎች ትሆናላችሁ?
ንጉሡ፥ “ስለ ልጁ አዝኖአል” መባሉን በዚያ ቀን ሠራዊቱ ሰምቶ ስለ ነበር፥ የዚያ ዕለት ድል በመላው ሠራዊት ዘንድ ወደ ኀዘን ተለውጦ ዋለ።
የኤፍሬም ሰዎች ኃይላቸውን አሰባስበው ወደ ጻፎን በመሻገር ዮፍታሔን፥ “አሞናውያንን ለመውጋት ስትወጣ አብረንህ እንድንሄድ ያልጠራኸን ለምንድን ነው? ቤትህን በላይህ ላይ እናቃጥለዋለን አሉት።”
በዚያን ጊዜ የኤፍሬም ሰዎች፥ “ምድያማውያንን ለመውጋት ስትሄድ ለምን አልጠራኸንም? ለምንስ እንዲህ ያለ ነገር አደረግህ?” በማለት ጌዴዎንን እጅግ ነቀፉት።