2 ሳሙኤል 18:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂውም ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጣ፤ ቀና ብሎም ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ሳለ፣ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ሲመለከት፣ አንድ ሰው ብቻውን ሲሮጥ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በከተማይቱ ውስጣዊና ውጫዊ በሮች መካከል ባለው ግልጥ ቦታ ተቀምጦ ነበር፤ ጠባቂው በቅጥሩ በኩል ወደ ማማው ወጥቶ ስለ ነበር ቀና ብሎ ሲመለከት አንድ ሰው ብቻውን እየሮጠ ሲመጣ አየ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ወጣ፤ ዐይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፥ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደበሩ ሰገነት ወጣ፥ አይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ። |
አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።
ንጉሡም፥ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው። ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ በመቶና በሺህ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ፥ ንጉሡ በቅጥሩ በር ቆሞ ነበር።
በል አሁን ተነሥተህ ውጣና አገልጋዮችህን አበረታታ፤ ባትወጣ ግን በዚች ሌሊት አንድም ሰው አብሮህ እንደማይሆን በጌታ ስም እምላለሁ፤ ይህ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከደረሰብህ ክፉ ነገር ሁሉ የባሰ መከራ ያሰከትልብሃል።”
እዚያ እንደደረሰም፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፥ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፥ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ።