2 ሳሙኤል 18:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽም እንደገና ኢዮአብን፥ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፥ “ልጄ ሆይ፥ የምሥራቹ ሽልማት እንደማያሰጥህ እያየህ መሄድ ለምን አስፈለገህ?” ብሎ መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደ ገና ኢዮአብን፣ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፣ “ልጄ ሆይ፣ መሄድ ለምን አስፈለገህ? ሽልማት የሚያሰጥህ ምን የምሥራች ይዘህ ነው?” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሒማዓጽም “የፈለገው ነገር ቢሆን ግድ የለኝም፤ ስለዚህ እኔም ወሬውን እንዳደርስ ፍቀድልኝ” አለ። ኢዮአብ ግን “ልጄ ሆይ፥ ስለምን ይህን ማድረግ ፈለግኽ? ይህን ስላደረግህ ምንም ሽልማት አታገኝም እኮ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማሖስ ኢዮአብን፥ “የሆነ ሆኖ ኩሲን ተከትዬ፥ እባክህ ልሩጥ” አለው። ኢዮአብም፥ “ልጄ ሆይ፥ ለምን ትሮጣለህ? ተመለስ፤ ብትሄድ ይች ወሬ ለጥቅም አትሆንህምና” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳግመኛም የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ ኢዮአብን፦ የሆነ ሆኖ ኵሲን ተከትዬ፥ እባክህ፥ ልሩጥ አለው። ኢዮአብም፦ ልጄ ሆይ፥ መልካም ወሬ የምትወስድ አይደለህምና ትሮጥ ዘንድ ለምን ትወድዳለህ? አለ። |
አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።
ንጉሡም፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀ። አሒማዓጽም፥ “ኢዮአብ የንጉሡን አገልጋይና እኔንም አገልጋይህን ሊልክ ሲል፥ ትልቅ ሁካታ አይቻለሁ፤ ምን እንደሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰ።
ንጉሡም “ስለምን ትሄዳለህ? ወደ አገርህ ለመሄድ ያሰብከው ከቶ ምን ጎድሎብህ ነው?” አለው። ሀዳድም “ምንም የተጓደለብኝ ነገር የለም፤ ብቻ ወደ ትውልድ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ” ሲል ለንጉሡ መለሰ፤