ኢዮአብም፥ “ዛሬ የምሥራቹን ወሬ የምትወስድለት አንተ አይደለህም፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ፥ ዛሬ ሳይሆን የምሥራቹን ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ” አለው።
2 ሳሙኤል 18:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፥ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው። ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዮአብ ለኢትዮጵያዊው፣ “ሂድና ያየኸውን ለንጉሡ ንገር” አለው፤ ኢትዮጵያዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዮአብ አገልጋዩ የነበረውን አንድ ኢትዮጵያዊ ጠርቶ “ያየኸውን ሁሉ ሄደህ ለንጉሡ ንገር” አለው፤ አገልጋዩም እጅ ነሥቶ ሮጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአብም ኩሲን፥ “ሂድ፤ ያየኸውንም ሁሉ ለንጉሥ ንገር” አለው። ኩሲም ለኢዮአብ ሰግዶ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአብም ኵሲን፦ ሂድ ያየኸውንም ለንጉሡ ንገር አለው። ኵሲም ለኢዮአብ እጅ ነሥቶ ሮጠ። |
ኢዮአብም፥ “ዛሬ የምሥራቹን ወሬ የምትወስድለት አንተ አይደለህም፤ የንጉሡ ልጅ ስለ ሞተ፥ ዛሬ ሳይሆን የምሥራቹን ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ” አለው።
የሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽም እንደገና ኢዮአብን፥ “የመጣው ይምጣ፤ እባክህ ኢትዮጵያዊውን ተከትየው ልሩጥ” አለው። ኢዮአብ ግን፥ “ልጄ ሆይ፥ የምሥራቹ ሽልማት እንደማያሰጥህ እያየህ መሄድ ለምን አስፈለገህ?” ብሎ መለሰለት።
አሒማዓጽም፥ “የመጣው ይምጣ፤ መሄድ እፈልጋለሁ” አለ። ስለዚህም ኢዮአብ፥ “ሩጥ!” አለው። ከዚያም አሒማዓጽ በሜዳው መንገድ ሮጦ ኢትዮጵያዊውን ቀድሞት ሄደ።