2 ነገሥት 14:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሀያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ከኢየሩሳሌም ይሆዓዲን ተብላ የምትጠራ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ከኢየሩሳሌም ይሆዓዲን ተብላ የምትጠራ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገሥም በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እናቱም ዮአድም የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። |
አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።
አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች።