ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በጌታ ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም በእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
2 ነገሥት 11:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮዳሄ፥ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን እንዲመሠረት አደረገ፤ እንደዚሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን መሠረተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮዳሄ፥ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ፥ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፤ ደግሞም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፤ ደግሞም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ። |
ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በጌታ ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም በእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኃላፊዎች ወደ ሆኑት የጦር መኰንኖች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸውና፥
ንጉሡ በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና ሐሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፥ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳኑን አደሰ፤ ስለዚህም በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም በቃል ኪዳኑ ተባበረ።
የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትም በኬብሮን በጌታ ፊት ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋር አደረገ፤ በሳሙኤልም አንደበት እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን ቀቡት።
ንጉሡም በስፍራው ቆሞ ጌታን ተከትሎ እንዲሄድ፥ ትእዛዛቱንና ምስክሩን ሥርዓቱንም በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ እንዲጠብቅ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል እንዲያደርግ በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።
ስለዚህ ከአምላካችን ጋር ቃል ኪዳን እናድርግ፥ ሚስቶችን ሁሉ ከእነርሱ የተወለዱትንም እንላካቸው፤ እንደ ጌታዬና በአምላካችን ትእዛዝ እንደሚንቀጠቀጡ ሕዝቦች ምክር፥ እንደ ሕጉም ይደረግ።
ከጌታ ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። ይህም ቃል የመጣው ለባርያዎች ስለ አርነታቸው አዋጅ እንዲነገር ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳን ካደረገ በኋላ ነው፤
ሳሙኤልም ለንጉሥ የሚገባውን ተግባርና ሥርዓት ለሕዝቡ ገልጦ ካስረዳ በኋላ በመጽሐፍ ጽፎ በጌታ ፊት አኖረው። ከዚህ በኋላ ሳሙኤል እያንዳንዱን ሰው ወደየቤቱ አሰናበተ።