በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው።
1 ሳሙኤል 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም፥ “መልካም፤ ና እንሂድ” አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “መልካም፤ ና እንሂድ” አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም አገልጋዩን “መልካም ነው እንሂድ!” አለው፤ ከዚያም የእግዚአብሔር ሰው ወደ አለበት ከተማ ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ብላቴናውን፥ “የተናገርኸው ነገር መልካም ነው፤ ና፤ እንሂድ” አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ብላቴናውን፦ የተናገረኸው ነገር መልካም ነው፥ ና፥ እንሂድ አለውና የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ከተማ ሄዱ። |
በዚህ ጊዜ የሳኦል አጎት እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበራችሁ?” ሲል ጠየቃቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ፍለጋ ሄደን ነበር፤ እንደማይገኙ በተረዳን ጊዜ ግን ወደ ሳሙኤል ሄድን” አለው።
በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው።
ቀደም ሲል በእስራኤል ዘንድ አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፥ “ኑ፥ ወደ ባለ ራእዩ እንሂድ” ይል ነበር፤ ዛሬ ነቢይ የሚባለው በዚያ ጊዜ ባለ ራእይ ይባል ነበርና።