1 ሳሙኤል 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋር ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያን ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት የምትመልሱ ከሆነ ከበደል መሥዋዕት ጋራ ስደዱት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፤ በዚያ ጊዜ ትፈወሳላችሁ፤ እጁም ከእናንተ ላይ ለምን እንዳልተነሣ ታውቃላችሁ” አሏቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት መልሳችሁ ለመላክ ብትፈልጉ፥ ስለ በደላችሁ የሚከፈል ስጦታ አብራችሁ መላክ ይገባችኋል፤ የቃል ኪዳኑ ታቦት ያለ ምንም ስጦታ ተመልሶ መሄድ የለበትም፤ በዚህም ዐይነት እናንተ ከሕመማችሁ ትፈወሳላችሁ፤ እርሱ እናንተን በብርቱ የቀጣበትንም ምክንያት ልታውቁ ትችላላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “የእስራኤልን አምላክ የቃል ኪዳኑን ታቦት ብትሰድዱአት ስለ አሳዘናችሁአት የበደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶዋን አትስደዱአት፤ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፤ ስርየትም ይደረግላችኋል፤ አለዚያ ግን የእግዚአብሔር እጅ ከእናንተ አይርቅም” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ የእስራኤልን አምላክ ታቦት ብትሰድዱ የበደል መሥዋዕት መልሱለት እንጂ ባዶውን አትስደዱት፥ የዚያን ጊዜም ትፈወሳላችሁ፥ እጁም ከእናንተ አለመራቁ ስለ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ አሉ። |
የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።
የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ካልዋጀኸው ግን አንገቱን ትሰብረዋለህ። የልጆችህንም በኩር ሁሉ ትዋጃለህ። በፊቴ አንድ ሰው ባዶ እጁን አይታይ።
ስለ ሠራው ኃጢአት ለጌታ የበደል መሥዋዕት ያመጣል፤ እርሱም ከመንጋው የበግ ወይም የፍየል እንስት ለኃጢአት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ኃጢአቱ ያስተሰርይለታል።
“በዓመት ሦስት ጊዜ ወንዶች ሁሉ በቂጣ በዓል፥ በመከርንና በዳስ በዓል፥ በአምላክህ በጌታ ፊት እርሱ በመረጠው ስፍራ ይታዩ፥ በጌታም ፊት ባዶ እጃቸውን አይታዩ።
የእግዚአብሔር እጅ በርትቶባቸው ስለ ነበር፥ ሞት ከተማዪቱን እጅግ አስደንግጧት ነበርና ሕዝቡ የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች በሙሉ ጠርተው፥ “የእስራኤልን አምላክ ታቦት ከዚህ አርቁልን፤ ወደ ገዛ ስፍራው ይመለስ፤ ያለበለዚያ እኛንም ሕዝባችንንም ይፈጃል” አሉ።
የአሽዶድ ሰዎች ይህን ባዩ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ጠንክሯልና የእስራኤል አምላክ ታቦት በእኛ ዘንድ መቆየት የለበትም” አሉ።
ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።
የጌታን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩ፤ ስለ በደልም መሥዋዕት ያቀረባችሁትን ልዩ ልዩ የወርቅ ዕቃ በሣጥን ውስጥ አድርጋችሁ በታቦቱ አጠገብ አኑሩት፤ መንገዱንም እንዲሄድ ልቀቁት።
ከዚያም ወዴት እንደሚሄድ ተመልከቱ፤ ወደ ገዛ አገሩ ወደ ቤትሼሜሽ አቅጣጫ የሚሄድ ከሆነ፥ ይህን ታላቅ መከራ ያመጣብን እርሱ ነው። ወደዚያ ካልሄደ ግን፥ መከራው በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የእርሱ እጅ እንዳልመታን እናውቃለን።”