ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
1 ሳሙኤል 6:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የቤትሼሜሽ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የቤትሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው ሲመለከቱም ታቦቱን በማየታቸው በጣም ደስ አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቤትሼሜሽም ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ቀና ብለው በተመለከቱም ጊዜ ታቦቱን አዩ፤ ያንንም በማየታቸው እጅግ ደስ አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤትሳሚስ ሰዎችም በእርሻ ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፤ ዐይናቸውንም ከፍ አድርገው የእግዚአብሔርን ታቦት አዩ፤ ደስ ብሎአቸውም ተቀበሉአት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤትሳሚስ ሰዎችም በሸለቆው ውስጥ ስንዴ ያጭዱ ነበር፥ ዓይናቸውንም ከፍ አድርገው ታቦቱን አዩ፥ በማየታቸውም ደስ አላቸው። |
ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።
ከዚያም ላሞቹ መንገዳቸውን በመያዝ፥ እምቧ እያሉ፥ ቀጥ ብለው ወደ ቤትሼሜሽ አመሩ። የፍልስጥኤም ገዢዎችም እስከ ቤትሼሜሽ ድንበር ተከተሏቸው።
ሠረገላውም ወደ ቤትሼሜሽ ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ ቆመ። በዚያ ስፍራ አንድ ትልቅ ቋጥኝ ነበር። ሕዝቡም የሠረገላውን ዕንጨት ፈለጡት፤ ላሞቹንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ለጌታ አቀረቡ።