1 ሳሙኤል 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር ተቀመጠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን ግዛት ሰባት ወር ቈየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፍልስጥኤም ሰባት ወር ከቈየ በኋላ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔርም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ሀገር ሰባት ወር ተቀመጠች። ምድራቸውም አይጦችን አወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ሰባት ወር ተቀመጠ። |
የአሽዶድም ሰዎች በማግስቱ ማለዳ ተነሥተው ሲመለከቱ እነሆ፥ ዳጎን በጌታ ታቦት ፊት መሬት ላይ በግንባሩ ተደፍቶ አገኙት። ከዚያም አንሥተው ዳጎንን ወደ ቦታው መለሱት።
ፍልስጥኤማውያን ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የጌታን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ ስፍራው እንዴት መመለስ እንደሚገባን ንገሩን” አሏቸው።