አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ።
1 ሳሙኤል 30:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ብሦር ተብሎ ከሚጠራው ወንዝ ሲደርሱ፤ ጥቂቶቹ በብሦር ወንዝ ቆዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊትና ዐብረውት የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ቦሦር ወንዝ መጡ፤ ጥቂቶቹም በቦሦር ወንዝ ቈዩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ ወጥተው ሄዱ፤ ብሦር ተብሎ በሚጠራው ወንዝ አጠገብ በደረሱ ጊዜ፥ ጥቂቶቹ በዚያ ዕረፍት በማድረግ ቈዩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረስም መጡ፤ ከእነርሱም የቀሩት በዚያ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፥ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረስም መጡ፥ ከእነርሱም የቀሩት በዚያ ተቀመጡ። |
አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ።