1 ሳሙኤል 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፥ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን ጌታ ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር አስተውሉ፤ ይህን ማድረግ አይገባችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞቼ ሆይ፤ የጠበቀን፣ የመጣብንንም ወራሪ በእጃችን የጣለልን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በሰጠን ነገር ይህን ማድረግ አይገባችሁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም “ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔር በሰጠን ድል እናንተ ይህን ማድረግ አትችሉም! እኛን በሕይወት ጠብቆ በወራሪዎች ላይ ድልን የሰጠን እርሱ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም አለ፥ “እግዚአብሔር አሳልፎ ከሰጠን በኋላ እንዲህ አታድርጉ፤ እርሱ ጠብቆናል፤ በእኛም ላይ የመጡትን ሠራዊት በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም፦ ወንድሞቼ ሆይ፥ የጠበቀን በእኛም ላይ የመጣውን ጭፍራ በእጃችን አሳልፎ የሰጠን እግዚእብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ አታድርጉ፥ |
ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።
የቤቱም ባለቤት ወደ ውጭ ወጥቶ እንዲህ አላቸው፤ “የለም ወዳጆቼ፤ እንዲህ አትሁኑ፤ ሰውየው እንግዳዬ ስለ ሆነ ይህን አሳፋሪ ድርጊት አትፈጽሙ።
ከዳዊት ተከታዮች ክፉዎቹና ምግባረ ቢሶቹ ግን፥ “አብረውን ስላልዘመቱ ካመጣነው ምርኮ አናካፍላቸውም፤ እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ብቻ ይዞ መሄድ ይችላል” አሉ።
ዳዊትም፥ “ይህን ወራሪ ሠራዊት ልከተለውን? እደርስባቸዋለሁን?” ሲል ጌታን ጠየቀ። ጌታም፥ “በእርግጥ ትደርስባቸዋለህ፤ ምርኮውንም ትመልሳለህ፤ ተከተላቸው!” ሲል መለሰለት።