በሌላ በኩል ደግሞ በነፍሴ ቆርጬ ሕይወቱን ባጠፋው ኖሮ፥ ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ነገር ስለ ሌለ፥ አንተም ራስህ በተነሣህብኝ ነበር” ብሎ መለሰለት።
1 ሳሙኤል 28:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋ ግን፥ “እነሆ፤ ሳኦል ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ እንዴት እንዳጠፋና ያደረገባቸውን ታውቃለህ፤ ታዲያ፥ ታስገድለኝ ዘንድ በሕይወቴ ላይ ወጥመድ የዘረጋኸው ለምንድን ነው?” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋ ግን፣ “እነሆ፤ ሳኦል ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ እንዴት እንዳጠፋና ያደረገባቸውን ታውቃለህ፤ ታዲያ፣ ታስገድለኝ ዘንድ በሕይወቴ ላይ ወጥመድ የዘረጋኸው ለምንድን ነው?” አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴትዮዋም “ንጉሥ ሳኦል ያደረገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህ፤ እርሱ እኮ ጠንቋዮችንና ሙታን ጠሪዎችን ከእስራኤል ምድር አጥፍቶአቸዋል፤ ታዲያ አንተ እኔን አጥምደህ ልታስገድለኝ የምትፈልገው ስለምንድን ነው?” ስትል መለሰችለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም፥ “እነሆ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር እንዳጠፋ ሳኦል ያደረገውን ታውቃለህ፤ ስለምን እኔን ለማስገደል ለነፍሴ ወጥመድ ታደርጋለህ?” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም፦ እነሆ፥ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ከምድር እንዳጠፋ ሳኦል ያደረገውን ታውቃለህ፥ ስለ ምን እኔን ለማስገደል ወጥመድ ለነፍሴ ታደርጋለህ? አለችው። |
በሌላ በኩል ደግሞ በነፍሴ ቆርጬ ሕይወቱን ባጠፋው ኖሮ፥ ከንጉሡ ተደብቆ የሚቀር ነገር ስለ ሌለ፥ አንተም ራስህ በተነሣህብኝ ነበር” ብሎ መለሰለት።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ “የሶርያ ንጉሥ ይህን ሰው እንደምፈውስለት አድርጎ እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከቆዳ በሽታ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? በእርግጥ ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ መፈለጉን በግልጥ ያሳያል!” አለ።
በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በራማ አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦልም ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባሯቸው ነበር።