ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼ አለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤
1 ሳሙኤል 28:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እባክህ አገልጋይህ የምትልህን ስማ፤ ብርታት አግኝተህ መሄድ እንድትችል፥ ጥቂት ምግብ ላቅርብልህና ብላ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም እባክህ አገልጋይህ የምትልህን ስማ፤ ብርታት አግኝተህ መሄድ እንድትችል፣ ጥቂት ምግብ ላቅርብልህና ብላ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ደግሞ አሁን የእኔን የአገልጋይህን ቃል ስማ፤ ምግብ ላዘጋጅልህና ተመገብ መንገድህንም በርትተህ መሄድ ትችላለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ አንተ ደግሞ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፤ በፊትህም ቁራሽ እንጀራ ላኑርልህ፤ መንገድም ትሄዳለህና ትበረታ ዘንድ ብላ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ አንተ ደግሞ የባሪያህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ፥ በፊትህም ቁራሽ እንጀራ ላኑርልህ በመንገድም ስትሄድ ትበረታ ዘንድ ብላ አለችው። |
ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ ሲንቀጠቀጥ ስላየችው እንዲህ አለችው፦ “እኔ አገልጋይህ የአንተን ቃል ሰምቼ ሕይወቴን እስከ ማሳለፍ ደርሼ አለሁ፤ ያልከኝንም ነገር አዳመጥኩ፤
እርሱም፥ “አልበላም” በማለት እምቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትዮዋ ጋር ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ። ከመሬትም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ።