ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት መንግሥትን ከሳኦል ቤት እንደሚወስድ ተስፋ ተሰጥቶታልና።”
1 ሳሙኤል 28:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በእኔ የተናገረውን አድርጓል፤ ጌታ መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በእኔ የተናገረውን አድርጓል፤ እግዚአብሔር መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእኔ አማካይነት የነገረህን ሁሉ እየፈጸመ ነው፤ መንግሥቱንም ከአንተ እጅ ወስዶ ለጐረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በቃሌ እንደ ተናገረ አድርጎአል፤ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለባልንጀራህ ለዳዊት ሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በቃሌ እንደ ተናገረ አድርጎአል፥ እግዚአብሔርም መንግሥትህን ከእጅህ ነጥቆ ለጎረቤትህ ለዳዊት ሰጥቶታል። |
ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ምድር ላይ የዳዊትን ዙፋን ለመመሥረት መንግሥትን ከሳኦል ቤት እንደሚወስድ ተስፋ ተሰጥቶታልና።”
ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የጌታ መንፈስ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ ራማ ተመለሰ።