ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
1 ሳሙኤል 28:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴትዮዋም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” ብላ ጠየቀችው። እርሱም፥ “ሳሙኤልን አስነሺልኝ” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴትዮዋም፣ “ማንን ላስነሣልህ?” ብላ ጠየቀችው። እርሱም፣ “ሳሙኤልን አስነሺልኝ” አላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ታዲያ ማንን ላስነሣልህ?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም “ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቲቱም፥ “ማንን ላስነሣልህ?” አለችው፤ እርሱም፥ “ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቲቱም፦ ማንን ላስነሣልህ? አለች፥ እርሱም፦ ሳሙኤልን አስነሽልኝ አለ። |
ሰዎች፤ የሚያነበንቡትንና የሚያንሾካሹኩትን ሟርተኞችንና መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ ቢሏችሁ፤ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን? በሕያዋን ምትክ ሙታንን መጠየቅ ለምን አስፈለገ?
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “አስነሥተህ የምታውከኝ ለምንድነው?” አለው፤ ሳኦልም፥ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ፍልስጥኤማውያን እየወጉኝ ነው፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቋል፤ በነቢያትም ሆነ በሕልም አልመለሰልኝም፤ ስለዚህ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ እንድትነግረኝ ጠራሁህ” አለው።