1 ሳሙኤል 24:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት የሳኦልን ልብስ ጫፍ በመቁረጡ ልቡ በኀዘን ተመታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰዎቹም፣ “እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና እግዚአብሔር የቀባው ስለ ሆነም እጄን በርሱ ላይ ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ተከታዮቹን “እግዚአብሔር ቀብቶ ባነገሠው በጌታዬ ላይ እጄን ከማንሣት እግዚአብሔር ይጠብቀኝ! እርሱ እግዚአብሔር የመረጠው ንጉሥ ስለ ሆነ እኔ በእርሱ ላይ ምንም ዐይነት ጒዳት ላደርስበት አይገባኝም!” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የሳኦልን የልብሱን ዘርፍ ስለ ቈረጠ የዳዊት ልብ በኀዘን ተመታ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹንም፦ እግዚአብሔር የቀባው ነውና እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር አደርግ ዘንድ እጄንም እጥልበት ዘንድ እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው አላቸው። |
ዳዊት ሕዝቡን ከቆጠረ በኋላ ኅሊናው ወቀሰው፤ ዳዊትም ጌታን፥ “ባደረግሁት ነገር የፈጸምኩት ታላቅ ኃጢአት ነው፤ አሁን ግን፥ ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን በደል ይቅር እንድትል እለምንሃለሁ፤ የፈጸምኩት ታላቅ የሞኝነት ሥራ ነውና” አለ።
የአዴር ልጅ እንዲህ ይላል፦ “ብርህና ወርቅህ ለእኔ ነው፥ ሴቶችህና መልካካሞቹም ልጆችህ ለእኔ ናቸው” ብሎ ወደ ከተማይቱ መልእክተኞችን ላከ።
እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”
ለሰዎቹም፥ “ጌታ በቀባው በጌታዬ ላይ እንዲህ ያለውን ነገር ከማድረግና ጌታ የቀባው ስለ ሆነም እጄን በእርሱ ላይ ከማንሣት ጌታ ይጠብቀኝ” አላቸው።