በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በሰዎች ሰይፍ ያልቃሉ።
1 ሳሙኤል 22:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ሳኦል የጌታን ካህናት እንደ ገደላቸው ለዳዊት ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ገደላቸው ለዳዊት ነገረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንዴት እንደ ፈጀም ለዳዊት ነገረው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ፈጀ ለዳዊት ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ፈጀ ለዳዊት ነገረው። |
በመሠዊያዬ ከምታገለግሉት ከእናንተ መካከል ሳላጠፋ የማስቀረው አንድ ሰው ዐይንህን በእንባ የሚያጠፋና ልብህን የሚያሳዝን ይሆናል፤ የቤተሰብህ አባሎች ሁሉ ግን በሰዎች ሰይፍ ያልቃሉ።
ዳዊትም አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ያን ዕለት ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያ ስለ ነበር፥ ነገሩን በትክክል ለሳኦል እንደሚናገር አውቄአለሁ፤ ለመላው የአባትህ ቤተሰብ ዕልቂት ተጠያቂው እኔ ነኝ።