1 ሳሙኤል 20:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታን፥ “ና! ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፤ ተያይዘውም ወጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታን፣ “በል ና፤ ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፤ ተያይዘውም ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታንም “ና! ወደ ሜዳ እንሂድ!” ሲል መለሰለት፤ ሁለቱም ወደ ሜዳ ወጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም ዳዊትን፥ “ና፤ ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው። ሁለቱም ወደ ሜዳ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም ዳዊትን፦ ና ወደ ሜዳ እንውጣ አለው። ሁለቱም ወደ ሜዳ ወጡ። |
ዮናታን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ምስክር ይሁን! ነገ በዚህ ሰዓት ወይም በሦስተኛው ቀን፥ ስለ አንተ መልካም አስተሳሰብ ያለው መሆኑን አባቴን ጠይቄ ከተረዳሁ በኋላ፥ ስለዚሁ ጉዳይ የሚገልጥልህ መልእክተኛ እልክብሃለሁ፤