የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፥ “አሒማዓጽና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቋት። ሴቲቱም፥ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
1 ሳሙኤል 19:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል ዳዊትን እንዲይዙት ሰዎች በላከ ጊዜ ሜልኮል፥ “እርሱ ታሟል” አለቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦል ዳዊትን እንዲይዙት ሰዎች በላከ ጊዜ ሜልኮል፣ “እርሱ ታሟል” አለቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሳኦል ወታደሮች ዳዊትን ለመያዝ በመጡ ጊዜ ሜልኮል እርሱ ታሞ ተኝቶአል አለቻቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ዳዊትን ይዘው እንዲያመጡት መልእክተኞችን ላከ፤ እርስዋም ታሞአል አለቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም ዳዊትን እንዲያመጡት መልእክተኞችን ላከ፥ እርስዋም፦ ታምሞአል አለቻቸው። |
የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፥ “አሒማዓጽና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቋት። ሴቲቱም፥ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
ስለዚህ ዳዊትን እንዲይዙ ሰዎችን ላከ፤ እነርሱም የነቢያትም ጉባኤ በሳሙኤል መሪነት ትንቢት ሲናገሩ ባዩ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል ሰዎች ላይ ወረደ፤ እነርሱም እንደዚሁ ትንቢት ተናገሩ።