በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፥ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ጌታ ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ።
1 ሳሙኤል 15:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ሳሙኤል አብሮት ተመለሰ፤ ሳኦልም ለጌታ ሰገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሳሙኤል ዐብሮት ተመለሰ፤ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሳሙኤል አብሮት ወደ ጌልጌላ ሄደ፤ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ከሳኦል በኋላ ተመለሰ፤ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ከሳኦል በኋላ ተመለሰ፥ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ። |
በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፥ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ጌታ ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ።
ሳኦልም መልሶ፥ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ ነገር ግን በሕዝቤ አለቆች ፊትና በእስራኤል ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለጌታ እሰግድ ዘንድ እባክህ አብረኸኝ ተመለስ” አለው።
ከዚያም ሳሙኤል፥ “የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ” አለ። አጋግም፥ “በውኑ ሞት እንዲህ መራራ ነውን?” በማለት እየተንቀጠቀጠ መጣ።