1 ሳሙኤል 13:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታን ጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፥ “ዕብራውያን ይስሙት!” በማለት በሀገሩ ሁሉ መለከት አስነፋ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታን ጌባዕ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሪቱ ሁሉ መለከት አስነፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናታን ጌባዕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ይህን ወሬ ሰሙ፤ ሳኦልም መልእክተኞችን ልኮ በሀገሩ ሁሉ እምቢልታ በማስነፋት ዕብራውያን ለጦርነት ጠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም በኮረብታው የነበሩትን የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ያን ሰሙ፤ ሳኦልም፦ እስራኤል ይስሙ ብሎ በሀገሩ ሁሉ ቀንደ መለከት ነፋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም በናሲብ ውስጥ የነበረውን የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ መታ፥ ፍልስጥኤማውያንም ያን ሰሙ፥ ሳኦልም፦ ዕብራውያን ይስሙ ብሎ በአገሩ ሁሉ ቀንደ መለከት ነፋ። |
በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሼባዕ የተባለ አንድ ከንቱ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
ምድር ሁሉ ከጌባ ጀምሮ በኢየሩሳሌምም ደቡብ በኩል እስካለችው እስከ ሬሞን ድረስ ተለውጣ፥ እንደ ዓረባ ትሆናለች፤ እርሷም ከፍ ከፍ ትላለች፥ ከብንያምም በር ጀምሮ እስከ ፊተኛው የበሯ ስፍራ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ፥ ከሐናንኤልም ግንብ ጀምሮ እስከ ንጉሡ መጥመቂያ ድረስ በስፍራዋ ትኖራለች።
ከዚያ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጦር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ጊብዓ ትሄዳለህ። ወደ ከተማዪቱ እንደ ደረስክም የነቢያት ጉባኤ በበገና፥ በከበሮ፥ በዋሽንትና በመሰንቆ ታጅበው ትንቢት እየተናገሩ ከማምለኪያው ኰረብታ ላይ ሲወርዱ ታገኛቸዋለህ።
ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ ነበሩ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች ግን በሚክማስ ሰፍረው ነበር፤